አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ እና ኪጋሊ ከተሞችን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የእህትማማች ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሩዋንዳ ዋና ከተማ ኪጋሊ ከንቲባ ዱሴምግዩንቫ ሳሙኤል ናቸው፡፡
በዋነኛነት ሁለቱ ከተሞች÷ በከተማ ልማት፣ በቆሻሻ አወጋጋድ፣ በወጣቶችና ስፖርት፣ በኢኮ ቱሪዝም፣ በትራፊክ ማኔጅመንት እና በአረንጋዴ ልማት ላይ በጋራ በሚሰሩበት አግባብ ላይ ከስምምነት መደረሱን ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታችንን ለማጠናከር በሚያስችሉን ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ብለዋል፡፡