ቢዝነስ

አየር መንገዱ የጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንጻና ድጋፍ ሰጪ መሰረተ ልማቶች አስመረቀ

By ዮሐንስ ደርበው

April 03, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንጻ እና ድጋፍ ሰጪ መሰረተ ልማቶች አስመረቀ፡፡

የተመረቀው መሠረተ-ልማት በ3 ሺህ 500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን÷ ይህም ወደ ከተማዋ የሚጓዙ መንገደኞችን ምቾት ከፍ ያደርገዋል መባሉን አየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለቱሪስት ፍሰቱ ዕድገትና ምቾትም የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ነው የተመላከተው፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ጌታቸው መንግስቴ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በከተማዋ የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ታወር ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ይታወቃል።