የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል መንግስትን የ30 ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ ዓውደ ርዕይ ተከፈተ

By Tamrat Bishaw

April 03, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስትን የ30 ዓመታት ጉዞ የሚያስቃኝ ዓውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከፍቷል።

በሥነ-ሥርዓቱ የክልልና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተዘጋጀው ዓውደ ርዕዩ እስከ መጪው ዓርብ ድረስ እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡

በመራኦል ከድር