አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቱ፣ በደሌ፣ ቡሌ ሆራ እና ደምቢዶሎ ከተሞች ሀገራዊ ለውጡንና ያመጣውን ውጤት የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ‘ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን” በሚል መሪ ሀሳብ ባካሄዱት የድጋፍ ሰልፍ የለውጡን ስኬቶች የሚመለከቱ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ለለውጡ አመራር ድጋፍ ማሳየታቸውን የዘገበው ኦቢኤን ነው፡፡
ሰልፈኞቹ ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በዚህም የወል አቅማችንን በማጎልበት ኢኮኖሚያችንን በጽኑ መሰረት ላይ እንገነባለን! ህብረብሔራዊነታችንን በማጠናከር ለሁሉም የምትመች ሀገር እንገነባለን! የሚሉና ሌሎች ሀገራዊ አንድነትን የሚያጸኑ መፈክሮችን በማሰማት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።