Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት 6 ዓመታት የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል መሠረት ተጥሏል – ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ዓመታት የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል መሠረት ተጥሏል ሲሉ የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) ገለጹ።

በሸገር ከተማ አስተዳደር ከለውጡ በኋላ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል የሚያግዝ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ እየተካሔደ የሚገኘው ‘ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ የወል አቅምን በማሳደግ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ይጠይቃል።

ባለፉት ስድስት ዓመታት የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል መሠረት ተጥሏልም ነው ያሉት ።

በዚህም በሸገር ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ከሀገራዊ ልማት ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ ገልጸው ÷ ይህን የተገኘውን ልማት ለማጽናት የሠላም ዘብ መሆን ያስፈልጋል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Exit mobile version