የሀገር ውስጥ ዜና

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ

By Amele Demsew

April 02, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በለውጡ የተገኙ ውጤቶችን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ ተካሂዷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ከተሞች ‘ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን” በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ነዋሪዎችም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና በለዉጡ መንግስት በሳል አመራር የተገኙ ለዉጦችን ለመደገፍና ለማስቀጠል ያለመ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሻምቡ ከተማ አካሂደዋል፡፡

አንዳንድ የድጋፍ ሰልፉ ታዳሚዎችም በጥቂት ዓመታት ዉስጥ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ድሎች መመዝገባቸዉን ጠቅሰዋል፡፡

እነዚህን አመርቂ ድሎች ሰላማችንን በማረጋገጥ እናስቀጥላለን ሲሉ ነዋሪዎቹ መናጋራቸውን የዘገበው ኦቢኤን ነው፡፡