የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማያ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ ተካሄደ

By Amele Demsew

April 02, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ማያ ከተማ በለውጡ የተገኙ ውጤቶችን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ ተካሂዷል፡፡

‘በምክክርና በመደማመጥ ሠላምን እናጸናለን’፣ ‘ድላችንን እንጠብቃለን’፣ ‘ለቀጣይ ስኬት በጋራ እንሰራለን’፣ ‘ለውጡን እናጸናለን’ እና ‘ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን’ የሚሉ መፈክሮች በሰላማዊ ሰልፉ ተንጸባርቀዋል ።

በድጋፍ ሰልፉ ከዞኑ የተለያዩ ወረዳዎችና ከማያ ከተማ የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

በምንያህል መለሰ