አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ መርማሪ ኮሚቴ በቅርቡ በሞስኮ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ በአሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡
“ዩክሬን አቀናብራዋለች ከተባለው ጥቃት ጋር በተያያዘ አሜሪካ እና ምዕራባውያን እጃቸው አለበት ወይ” የሚለውን ለማረጋገጥ ምርመራ መጀመሩን ኮሚቴው ዛሬ አስታውቋል፡፡
በዚሁ መሠረትም አሜሪካ እና ምዕራባውያን የተፈጸመውን ጥቃት በማደራጀት፣ በገንዘብ በማገዝ እና ጥቃቱ አንዲፈፀም ትዕዛዝ በመስጠት መሳተፋቸውን እና አለመሳተፋቸው እንደሚያረጋገጥ ገልጿል፡፡
ከሣምንት በፊት በሞስኮ በአንድ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ140 የሚልቁ ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ከ100 በላይ መቁሰላቸውን አስታውሶ አር ቲ ዘግቧል፡፡
ከጥቃቱ ጋር በተያያዘም ሩሲያ 12 የኢስላማዊ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን እና በአራት ተጠርጣሪዎች ላይም የሽብር ክስ መመስረቷ ይታወሳል፡፡