ስፓርት

አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ አቻ ተለያዩ

By Amare Asrat

March 31, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም አርሴናል በ65 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሲቲ ደግሞ በ64 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡

ቀደም ሲል ብራይተንን 2 ለ 1 ያሸነፈው ሊቨርፑል በ67 ነጥብ ሊጉን መምራት ጀምሯል፡፡