ስፓርት

በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

By Feven Bishaw

March 30, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት አሸንፈዋል፡፡

በዚህም ማርታ አለማየሁ አንደኛ፣አሳየች አይቸው ሁለተኛ እንዲሁም ሮቤ ዲዳ ሶስተኛ ሆነው በመግባት የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡

 

በተመሳሳይ በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት መዝገበ ስሜ የብር ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡