የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

By Amele Demsew

March 30, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረንስ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ÷ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል፡፡

“ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ የሚገኘው ኮንፈረንሱ÷ ከመጋቢት 21 እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በመድረኩም ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ውይይት ይደረጋል መባሉን በብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡