አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ባንክ ከኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ የ90 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የአክሲዮን ግዥ ፈጽሟል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጫንያለው ደምሴ÷ አማራ ባንክ ከባንክ ባሻገር ብሎ ሲነሳ በልዩ ልዩ ዘርፎች ተሳትፎ እንደሚያደርግ ለመግለጽ ነው፤ ይህ ስምምነትም ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።
ለሀገር ትልቅ ፋይዳ በሚኖረው የካፒታል ገበያ ባንኩ መሳተፉ ለቀጣይ እድገት የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ አማራ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ነዋይ ገበያ መሳተፍ መቻሉ አስደሳች ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡