አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 775 የላብራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 156 ደርሷል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 85 ወንዶች እና 51 ሴቶች ሲሆኑ ከ1 እስከ 97 የእድሜ ክልል የሚገኙ 124 ኢትዮጵያዊያን እና 12 የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው።
115 ከአዲስ አበባ ፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ 7 ከትግራይ ክልል ፣ 2 ከሀረሪ ክልል ፣ 2 ከአፋር ክልል እና 1 ሰው ከደቡብ ክልል ናቸው።
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 17ሰዎች 8 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከአማራ ክልል፣ 2 ከአፋር ክልል እና 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 361 ደርሷል።