የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ጠንካራ ብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ከገነቡ ሀገራት አንዷ ሆነች

By Amele Demsew

March 24, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጠንካራ ብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ከገነቡ ስድስት የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

መንግሥት አስፈላጊውን በጀት መድቦ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማትን መገንባት መቻሉ እና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን መሥራቱ ለስኬቱ መገኘት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም መንግሥት ለአሠራር ሥርዓት ዝርጋታ ልዩ ትኩረት መስጠቱ ለውጤቱ መገኘት ከፍተኛ ሚና አበርክቷል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡