የሀገር ውስጥ ዜና

ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች በሀገራችን ኢኮኖሚ የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Feven Bishaw

March 22, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ማኀበረሰብ በተለይም ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች በሀገራችን ኢኮኖሚ የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ዛሬ ከታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር በጠቃሚ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ “የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ማኀበረሰብ በተለይም ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች በሀገራችን ኢኮኖሚ የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ነው” ብለዋል።

ዛሬ ጠዋት ከነዚህ ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር በጠቃሚ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል ሲሉኝ መልዕክት አስተላልፈዋል።