አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የታገዱ የሩሲያ ንብረቶች ላይ የአውሮፓ ህብረት የያዘውን ዕቅድ አውግዛለች፡፡
ክሬምሊን የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን ለዩክሬን የጦር መሳሪያ መግዣነት እንዲውሉ ያቀረቡት ሀሳብ የዓለም አቀፍ ህግን መሰረት የዘነጋ ነው ብሏል።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ አውሮፓውያን የያዙት ዕቅድ ስማቸውን በማጠልሸት የሚያደርሰውን ጉዳት ያውቁታል ብለዋል።
ስለ ቦሬል ዕቅድ የተጠየቁት የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በበኩላቸው “ይህ በቀላሉ ዝርፊያ ነው” ሲሉ መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።