የሀገር ውስጥ ዜና

ወርቅን ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባትየሚያስችል ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ

By Amele Demsew

March 19, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወርቅ ሃብትን በህጋዊ መንገድ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት የሚያስችል ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ወርቅ አምራቾች ገለጹ፡፡

በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ የተመራ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች የክትትልና ድጋፍ ቡድን በጋምቤላ ክልል በሉንጋ ቀበሌ የወርቅ ማዕድን ልማትን ጎብኝቷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት ÷በክልሉ የሚገኘውን የወርቅ ምርት ለማሳደግና ህገወጥነትን ለማስቀረት በየመዋቅር ያሉ የመንግስት አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል፡፡

አቶ ገብረ መስቀል ጫላ በበኩላቸው÷ በክልሉ ያለው የማዕድን ሀብት በአግባቡ አልምቶ ለሀገር ልማት እንዲውል የተጠናከረ ስራ ይጠይቃል።

በተለይም ህገ ወጥ ነጋዴዎችን በመቆጣጠር እንዲሁም የወርቅ መጠንን በመጨመር ዘርፉን ማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የወርቅ ሀብቱን በህጋዊ መንገድ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት እንዲቻል ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ እንዳለበትም የክልሉ አንዳንድ የወርቅ ባለሃብቶች ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም መንግስት ለወርቅ እጥበት የሚመች የውሀ አማራጭና የተሽከርካሪ ነዳጅ እጥረትን እንዲፈታላቸው መጠየቃቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡