አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖቲንግሃም ፎረስት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የፋይናንሺያል ጨዋነት ሕግ ተላልፏል በሚል አራት ነጥብ ተቀነሰበት፡፡
ቡድኑ ሕጉን በመተላለፍ ፕሪሚየር ሊጉ ትርፋማ እንዳይሆን ማድረጉም በገለልተኛ አጣሪ ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡
ይህን ተከትሎም ቡድኑ አራት ነጥብ ተቀንሶበት ነጥቡ ከ25 ወደ 21 ዝቅ ብሏል፡፡
ኖቲንግሃም ፎረስት ከኤቨርተን በመቀጠል በውድድር ዓመቱ በፋይናንሺያል ጨዋነት ሕግ መተላለፍ ምክንያት ቅጣት የተጣለበት ቡድን ሆኗል፡፡