አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።
በመጪው ሐምሌ ወር የሚካሄደውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ ሀገራዊ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራት ንቅናቄ መጀመሩ ይታወቃል።
በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ መነሻ በማድረግ የተጀመረው ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በአፋር ክልሎች ቀጥሎ ነው ዛሬ በኦሮሚያ ክልል የተካሄደው።
በመርሐ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በሥነ -ሥርዓቱ ማጠናቀቂያ ላይም የአማራ ክልል ከኦሮሚያ ክልል የኦሎምፒክ ችቦ ተረክቧል።
በወርቅነህ ጋሻው