Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ 9 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እየተሠራጨ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ አሁን 9 ሚሊየን 209 ሺህ 631 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሩ እየተሠራጨ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በ2016/17 ዓ.ም የምርት ዘመን ከውጭ ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ 9 ሚሊየን 835 ሺህ 606 ኩንታል ጂቡቲ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ማዳበሪያ የማጓጓዝ ሥራው መጠናከሩን የገለጸው ኮርፖሬሽኑ÷ 440 ሺህ ኩንታል ዩሪያ የጫነች መርከብ ጂቡቲ ወደብ መድረሷን ጠቁሟል፡፡

ከአምስት ቀናት በኋላም 822 ሺህ 773 ኩንታል ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጂቡቲ ወደብ እንደምትደርስ ይጠበቃል ብሏል፡፡

ይህን ተከትሎም ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ከአምስት ቀናት በኋላ ወደ 10 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ከፍ እንደሚል አመላክቷል፡፡

Exit mobile version