አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡
በዚሁ መሠረትም አርሰናል ከባየርን ሙኒክ ጋር የሚገናኙ ይሆናል፡፡
እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ከቦርሲያ ዶርትመንድ፤ ሪያል ማድሪድ ደግሞ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ተድልድለዋል፡፡
በተጨማሪም ፓሪሴንት ዠርሜይን ከባርሴሎና ጋር በሩብ ፍፃሜው የሚገናኙ ይሆናል፡፡
በጥሎ ማለፉም የአርሰናል እና ባየርን ሙኒክ ጨዋታ አሸናፊ÷ከሪያል ማድሪድ እና ማንቼስተር ሲቲ አሸናፊ ጋር የሚፋለም ይሆናል፡፡
የቦርሲያ ዶርትመንድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ አሸናፊ ደግሞ ከባርሴሎና እና ፒ ኤስ ጂ አሸናፊ ጋር ይገናኛል፡፡
የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታም በፈረንጆቹ ሚያዝያ 9 እና 10 የሚደረግ ሲሆን÷ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ሚያዝያ 16 እና 17 የሚካሄድ መሆኑን ዛሬ የወጣው የጨዋታ መርሐ-ግብር አመላክቷል፡፡