ቴክ

በሁዋዌ የአይሲቲ አህጉራዊ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች 3ኛ ደረጃን ያዙ

By Mikias Ayele

March 15, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተኒዚያ በተካሄደው የሁዋዌ የአይሲቲ ክፍለ አህጉራዊ ፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

በ”ኮምፒውቲንግ ትራክ” በተደረገው ውድድር ከኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ የተወጣጡ 90 ተማሪዎች በተለያዩ ዘርፎች ተሳትፈዋል።

በውድድሩ የኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ቡድን አባላት ሞሮኮ እና ቱኒዚያን ተከትለው ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል።

በውድድሩ ሶስተኛ ደረጃን የያዙት ተማሪዎች የሁዋዌ ዘመናዊ ስልክ የተሸለሙ ሲሆን÷ ሌሎች 6 ተማሪዎች ደግሞ በተሳትፏቸው የሁዋዌ ታብሌቶችን ተሸልመዋል።

ከሦስቱ ተማሪዎች ሁለቱ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተማሪዎች ሲሆኑ÷ አንደኛው ተማሪ ደግሞ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አሸናፊዎች በ2024 በቻይና በሚካሄደው እና ከ500 ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች በሚሳተፉበት የመጨረሻው ምዕራፍ ውድድር ላይ የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል።

ከተማሪዎች በተጨማሪም ኩባንያው ለተማሪዎቻቸው ድጋፍ ላደረጉ መምህራን እውቅና መስጠቱ  ተመላክቷል።