የሀገር ውስጥ ዜና

የኢንዱስትሪ ባህል ግንባታን ታሳቢ ያደረገ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

By Amele Demsew

March 14, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ባህል ግንባታን ታሳቢ ያደረገ የምክክር መድረክ “የኢንዱስትሪው ማህበረሰብ ምክክር ለምርታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ከኢንዱስትሪው ማህበረሰብ ጋር እየተካሄደ ያለውን ይህንን የምክክር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ያዘጋጀው የስራና ህክህሎት ሚኒስቴር ነው፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዳንኤል ተሬሳ በወቅቱ እንዳሉት÷ በአሰሪና ሰራተኞች መካከልየሚደረግ ምክክር በኢንዱስትሪ ውስጥ የሚከሰት አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ በመፍታት በኩል ፋይዳው የጎላ ነው፡፡

በተጨማሪም÷ ለምርታማነት እንዲሁም ለአዲስ ኢንዱስትሪ ባህል ግንባታ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ እና የሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመድረኩ ከአዲስ አበባ፣ ከሲዳማና ከኦሮሚያ የተውጣጡ 400 የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ አባላት እየተሳተፉ እንደሆነ ተገልጿል።

በፈትያ አብደላ