አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 15 ሰዎችን ጭኖ የነበረ የሩሲያ ወታደራዊ መጓጓዣ አውሮፕላን መከስከሱ ተነገረ።
አውሮፕላኑ ከሞስኮ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በኢቫኖቫ ክልል አየር ላይ እያለ በእሳት ከተያያዘ በኋላ የመከስከስ አደጋ እንዳጋጠመው ተገልጿል።
አይኤል-76 የተሰኘው አውሮፕላን በውስጡ ስምንት የበረራ ሰራተኞችና ሰባት ተጓዦችን ይዞ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን÷ አንደኛው የሞተር ክፍሉ በእሳት ተያይዞና ከባድ የሆነ ጥቁር ጭስ ማውጣቱ በማህበራዊ ሚዲያ የወጡ ምስሎች አመላክተዋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አደጋው ማጋጠሙን ያረጋገጠ ቢሆንም ስለደረሰው ጉዳት ያለው ነገር አለመኖሩን ዲፌንስ ብሎግ ዘግቧል።