የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የላስካ ጤና ጣቢያን መርቀው ከፈቱ

By Meseret Awoke

March 09, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የላስካ ጤና ጣቢያን መርቀው ከፍተዋል፡፡

አቶ ጥላሁን ከበደ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የላስካ ጤና ጣቢያን መርቀው የከፈቱ ሲሆን ፥ በቆይታቸውም ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፍሬው ፍሻለው(ኢ/ር) እንደገለጹት ፥ ጤና ጣቢያው የአካባቢውን ነዋሪ ጥያቄ መሰረት ተደርጎ በመንግስት ድጋፍ በአንድ ዓመት ውስጥ የተገነባ ነው።

ጤና ጣቢያው በአካባቢው ከሕክምና አገልግሎት ጋር ሲነሳ የቆየው ችግር ለመፍታት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የባስኬቶ ዞን አስተዳደር ህንፃ ለመገንባት የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጣቸውም ተጠቁሟል፡፡

በኢብራሂም ባዲስ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!