Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስኮትላንድ ግላስኮው በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ።

የባህልና የስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለልዑኩ አቀባበል አድርገውለታል።

በውድድሩም ኢትዮጵያ በሁለት የወርቅ፣ በአንድ የብርና በአንድ የነሐስ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።

ኢትዮጵያ በ800 ሜትር ሴቶች በፅጌ ዱጉማ እና በ1 ሺህ 500 ሜትር በፍሬወይኒ ኃይሉ የወርቅ ሜዳሊያ፤ በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የብር እንዲሁም በ3 ሺህ ሜትር ወንዶች በሰለሞን ባረጋ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

ከአቀባበሉ በኋላም ዕውቅና የመስጠት ሥነ-ሥርዓት እንደሚካሄድ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።14:35

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version