አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ 38 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) መትታ መጣሏን አስታውቃለች፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ÷ የዩክሬን ጦር በክሬሚያ ደቡብ ምስራቅ ግዛት በምትገኘው ፊዮዶሲያ ከተማ ዛሬ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል፡፡
ይሁን እንጂ ሚኒስቴሩ በፊዮዶሲያ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት የደረሰውን ጉዳት መጠን አስመልከቶ ያለው ነገር አለመኖሩ ተመላክቷል፡፡
የሩሲያ ጦር በወሰደው አጸፋዊ እርምጃም 38 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉ ነው የተገለጸው፡፡
ከጥቃቱ ጋር ተያይዞም ክሬሚያን ከሩሲያ ጋር የሚያገናኘው ድልድይ በጊዜያዊነት መዘጋቱን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል፡፡
ዩክሬን ጥቃቱን የፈጸመችው አውሮፓውያን አጋሮቿን ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እየጠየቀች ባለችበት ወቅት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡