የሀገር ውስጥ ዜና

ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ የሕብረተሰብ ተወካዮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

By Melaku Gedif

March 03, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሲዳማ ፣ ደቡብ ምዕራብ ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የተውጣጡ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ድል የሆነው የዓድዋ ድል እጅግ ባማረና ሁሉንም በሚወክል መልኩ በመደራጀቱ እንደተደሰቱ ጎብኚዎቹ  መናገራቸውን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡