አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃማስ ልዑካን ቡድን አባላት የተኩስ አቁም ድርድር ለማድረግ ግብፅ ካይሮ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡
በድርድሩ ለስድስት ሣምንታት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ይደረሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡
የእስራኤልና ሃማስ ድርድር በሚቀጥሉት ከ24 አስከ 48 ሰዓታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንደሚከናወን ነው የተገለጸው፡፡
ይህን ተከትሎም በድርድሩ የሚሳተፉ የአሜሪካ፣ ኳታር እና ሃማስ ልዑካን ካይሮ መግባታቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡
የሃማስ ተደራዳሪዎች እንዳሉት ፥ እስራኤል ወታደሮቿን ከጋዛ ማስወጣትን ጨምሮ የሰብዓዊ እርዳታን ለማጠናከር ፈቃደኛ ከሆነች ስምምነት ላይ ለመድረስ መንገድ ይከፍታል፡፡
ሆኖም በጋዛ የሚገኘው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሰዓታት በፊት ባወጣው መረጃ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ቢያንስ 90 ፍልስጤማውያን ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ከኳታር ጋር ውይይቱን ሲመሩ የቆዩት የግብፅ ባለስልጣናት የሃማስ እና የእስራኤል ልዑካን በድርድሩ ላይ ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡
በሰሜናዊ ጋዛ የረሃብ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ከእርዳታ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ግፊት መጨመሩ በዘገባው ተጠቁሟል፡፡
የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት አምስት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን ፥ በዚህም ከ30 ሺህ 320 በላይ ፍልስጤማውያን ሕይዎት ሲነጠቅ ከ71 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በአንጻሩ በእስራኤል በኩል በጦርነቱ ከ1 ሺህ 400 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
#Israel #Hamas
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!