የሀገር ውስጥ ዜና

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸው 463 ተማሪዎች አስመረቀ

By Shambel Mihret

March 03, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 463 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር) እና የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ከተመራቂዎች መካከል 131 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን አስተምሮ ሲያስምርቅ የዛሬው ለ12ኛ ጊዜ ነውም ተብሏል፡፡