Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ንብረትነቷ የእንግሊዝ የሆነች መርከብ ቀይ ባህር ውስጥ መስጠሟ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ንብረትነቷ የእንግሊዝ የሆነች ዕቃ ጫኝ መርከብ በሁቲ አማፂያን በተሰነዘረባት ጥቃት ጉዳት ደርሶባት ቀይ ባህር ውስጥ መስጠሟ ተገልጿል፡፡
 
በኢራን የሚደገፈው የሚሊሺያ ቡድን በፈረንጆቹ ህዳር ወር የንግድ መርከቦችን ኢላማ ማድረግ ከጀመረ ወዲህ መርከብ ሲሰጥም ይህ የመጀመሪያው እንደሆነ ታምኖበታል፡፡
 
የእንግሊዝ ንብረት የሆነችው እቃ ጫኝ መርከብ ባለፈው ወር በሁቲዎች ጥቃት ጉዳት ከደረሰባት በኋላ በቀይ ባህር መስጠሟን የየመን መንግስት ማስታወቁ ተነግሯል።
 
መንግስት በሰጠው መግለጫም መርከቧ ዓርብ ምሽት ላይ መስጠሟን በመግለፅ አካባቢያዊ ጉዳት እንዳይከሰት ማስጠንቀቁም ተመላክቷል።
 
የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ መርከቧ ጥቃት በደረሰባት ወቅት 41 ሺህ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጭና እንደነበር ቀደም ሲል ማስታወቁን ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version