የሀገር ውስጥ ዜና

የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በድምቀት ተከበረ

By Mikias Ayele

March 02, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች በድምቀት ተከበረ፡፡

በዓሉ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በአማራ፣ አፋር፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪ እና ሌሎች ክልሎች በድምቀት ተከብሯል፡፡

በአከባበሩ ላይም የየአካባቢዎቹ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ ዓርበኞች፣ ወጣቶች፣ የፀጥታ አካላት እና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በዓሉ የተከበረው “ዓድዋ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡