የሀገር ውስጥ ዜና

ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ሐውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

By ዮሐንስ ደርበው

March 02, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ ሐውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ፡፡

የአበባ ጉንጉኑን ያስቀመጡት÷ የፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጀነራል አለምሸት ደግፌ፣ የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግስቴ እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዓርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ናቸው፡፡

በተጨማሪም አፈ-ጉባዔ አገኘሁ በቅርቡ በተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው ፓንአፍሪካዊነት ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ