የሀገር ውስጥ ዜና

የዓድዋ ንቅናቄ መድረክ የማጠቃለያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

March 01, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ዓድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ’ በሚል ሲካሄድ የቆው ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ የማጠቃለያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም በመድረኩ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወከሉ ሰዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የንቅናቄ መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርትና ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ለሳምንታት በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በበረከት ተካልኝ