አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችን ከመከላከል አንጻር የፋይናንስ ተቋማትና ባንኮች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡
እነሱም፡-
● ለደንበኞቻቸው ስለማጭበርበር ማስተማር ወይም ማሳወቅ- የደንበኞቻቸው የሳይበር ደህንነት ንቃት ከፍ ለማድረግ የተለያዩ መንገዶች በመጠቀም ተደራሽ ማድረግ፤
● ኤስ ኤምኤስ ወይም ገፊ ማሳወቂያዎች- ባንኮች ለደንበኞቻቸው የይለፍ ቃልን ሲያስገቡ ወይም የክፍያ ሙከራቸውን እንዲያረጋግጡ የሚጠይቅ ማሳወቂያ ወደ ስልካቸው፣ በኢ-ሜይላቸው እንዲደርሳቸው ማድረግ፤
● ደንበኞች ግብይት (ክፍያዎች በሚፈፅሙበት ጊዜ ወዲያውኑ በፍጥነት ክፍያ) ግብይት እንደፈፀሙ የሚያሳውቁ መልዕክቶች ወደ ስልካቸው እንዲደርሳቸው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤
● ባንኮች (የገንዘብ ዝውውር አገልግሎት ሰጪዎች) መተግበርያዎቻቸው ውስጥ in-app Multi-factor Authentication functionality ማካተት ይኖርባቸዋል::
ለምሳሌ አካላዊ መለያ የጣት የአሻራና የመሳሰሉትን…
● ሞባይል መተግበርያዎቻቸው በየጊዜው የደህንነት ተጋላጭነት ሙከራ ማድረግ፤
● ኢንክሪፕሽን፡- የሞባይል ባንኪንግ መተግበርያዎች ሚስጥራዊ መረጃዎች እንደ ሎጊን መረጃ፣ የባንክ መግለጫዎች መመስጠርና መደበቅ ማስቻል አለባቸው፤
● በየወቅቱ እየተቀያየሩ የሚመጡ የማጥቂያ ወይም የማጭበርበርያ መንገዶችን በመከታተል መፍትሄዎችን መስጠት እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡
ቀደም ብሎ ተደራሽ ባደረግነው ጽሁፍ በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የሚፈጸሙ ማጭበርበሮች እንዲሁም የመከላከያ መንገዶችን አስመልክቶ ይሄን ሊንክ https://www.fanabc.com/archives/236212 በመጠቀም ያንብቡ፡፡