የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያ የ46 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

February 29, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ፈንድ ዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮጵያ የ46 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታውቋል፡፡

ድጋፉ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ለሚኖሩ አርብቶ አደሮች ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ድጋፉ በአካባቢው የውሃ ማሰራጫ መሰረት ልማቶችን እና የውሃ አቅርቦት መጠን ለማሳደግ እንደሚያስችል ነው የተነገረው፡፡

በዚህም ዘጠኝ የሚደርሱ የውሃ ማጠራቀሚያዎችን እና 142 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የውሃ ማሰራጫ መስመሮችን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ- ልማቶች እንደሚገነቡ የተቋሙ መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህም በቦረና ዞን በሚከሰተው ድርቅ ሊፈጠር የሚችልን የውሃ እጥረት ለመቋቋም ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia #Africa #Borena

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!