አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን ሀገራት ወታደሮቻቸውን ወደ ዩክሬን እንዳይልኩ አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ሁለት ሣምንት በቀረው የ2024 የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዋዜማ በሀገሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ዙሪያ ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም ፥ ‘‘ምዕራባውያን በዩክሬን እና በሌሎች በርካታ ሀገራት ላይ እንዳደረጉት ሩሲያን ወደ ከሸፈች ሀገርነት ለመቀየር አስበዋል’’ ብለዋል።
’’የቅኝ ግዛት እና በዓለም ላይ ብሔራዊ ግጭቶችን የመቀስቀስ ልማድ ያላቸው ምዕራባውያን ልማትን ከማደናቀፍ የዘለለ ዓላማ አላቸው’’ ሲሉም ነው የተናገሩት።
በሩሲያ ምትክ የፈለጉትን ማድረግ የሚችሉበት ጥገኛ ፣ ደካማ እና የደቀቀ ሀገር ነው ሲሉም አክለዋል።
የውጭ ስጋቶችን በመጋፈጥ ሀገሪቱን የሚከላከለው የሩሲያ ህዝብ እና ብሔራዊ አንድነቱ ነው ያሉት ፑቲን ፥ መንግሥት የብሔራዊ ሉዓላዊነት መሠረት የሆኑ ተቋማትን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበትም አንስተዋል።
በዚህም በሀገር ውስጥ ጉዳያችን ማንም ጣልቃ እንዲገባ አንፈቅድም ማለታቸውን የዘገበው አር ቲ ነው።
ሩሲያ በትናንትናው ዕለትም የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወታደሮች በዩክሬን የሚሰማሩ ከሆነ ዓለም እጅግ ውስብስብ ሁኔታ ልታስተናግድ እንደምትችል ማስጠንቀቋ አይዘነጋም።
#Russia #Ukrain
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!