የሀገር ውስጥ ዜና

ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የልማትና የሰብዓዊ ሥራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

By Melaku Gedif

February 29, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ ) የሰብዓዊ እርዳታ ምላሽና አቅርቦት ም/ዋና ዳይሬክተር ኢድዋርድ ቻይበን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ ወቅታዊ የልማት ሁኔታ እና የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ የሚያጋጥሙ አስቸኳይ ችግሮችን ለመፍታት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ መወያየታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ዓለም አቀፍ አጋር አካላት በድርቅና ሌሎች ችግሮች ሳቢያ እርዳታ ለሚሹ ወገኖች አፋጣኝ የሰብዓዊ እርዳታ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ኢድዋርድ ቻይበን÷ ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ልማትን ለማፋጠን እና የሰብዓዊ እርዳታን ለማዳረስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!