የሀገር ውስጥ ዜና

በ50 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባ የሎጂስቲክስ አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ ቴክኖሎጂ ተመረቀ

By Meseret Awoke

February 29, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ50 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው የሎጂስቲክስ አገልግሎትን ቀልጣፋ ያደርጋል ተብሎ የታመነበት ቴክኖሎጂ ተመርቋል፡፡

ቴክኖሎጂው ለኢ-ኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎትን ቀልጣፋ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል፡፡

ይህም የአገልግሎት ዘርፉን አንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋልም ነው የተባለው፡፡

ቴክኖሎጂው፥ የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት አሰራርን ዘመናዊ የሚያደርግና ከሰው ንክኪ ነፃ የሆነ ነው ተብሏል፡፡

ድካምን የሚያቀልና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጠው ቴክኖሎጂ በ50 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

የምረቃ መርሐ-ግብሩ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል::

በዘቢብ ተክላይ

#Ethiopia #Technology #logistics

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!