የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት ባለሃብቶች ሰላምን ለማረጋገጥ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

By Melaku Gedif

February 29, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር በክልሉ ሰላም እና ልማት ዙሪያ እየተወያዩ ነው፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ÷ በክልሉ ባለፉት 8 ወራት በነበረው ግጭት ከፍተኛ የሰብዓዊ ጉዳት እና የክልሉ ሕዝብ ሃብት የሆኑ ንብረቶች መውደማቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የማኅበረሰቡ የረጅም ዘመናት የማንነት መገለጫ የሆኑ የጋራ ትስስር እሴቶች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል ነው ያሉት፡፡

ውይይቱ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስገንዘብ በአማራ ክልል የኢኮኖሚ እድገት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ባለሃብቶች ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ነው መባሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡