የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር በበጋ መስኖ ስንዴ መልማቱ ተገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

February 28, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጋ መስኖ ስንዴ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር በመስኖ ስንዴ መልማቱን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

አቶ ሽመልስ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከ105 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡

ከከባቢ ሁኔታ ወሳኝነትና ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ የተጀመሩ ሥራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

ጎን ለጎንም ባመረትነው ልክ የመቆጠብ እንቅስቃሴውን አጠንክረን እንቀጥላለን ብለዋል።