የሀገር ውስጥ ዜና

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከዩኒሴፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

February 28, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማ ከዩኒሴፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቴድ ቻይባን ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይታቸውም፥ በተለያዩ ችግሮች በተጎዱ አካባቢዎች ያለውን የጤና ስርዓት ማጠናከር የሚቻልበትን ሁኔታ ዳስሰዋል፡፡

በተጨማሪም ተደራሽ ባልሆኑ አካባቢዎች ህጻናትን ከተለያዩ በሽታዎች ለመጠበቅ በሚቻልባቸው የክትባት ንቅናቄዎች ዙሪያ መምከራቸውን ከዩኒሴፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia #UNICEF

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!