አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ም/ቤት እና የፌዴራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት÷የተቋማቱ በጋራ መስራት ም/ቤቱ ሕገ-መንግስቱን በመተርጎም ሒደት ውስጥ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ለመፍታት ያስችለዋል።
የሃብት አስተዳደርና የበጀት ክፍፍል ሥራው ውጤታማ እንዲሆን እንደሚያግዝ ጠቁመው÷ ከማንነትና ወሰን ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን በጥናት ተመስርቶ ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችልም ገልጸዋል፡፡
የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በበኩላቸው÷ ኢንስቲትዩቱ በአቅም ግንባታ ላይ ሰፊ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱ እውነተኛ ፌዴራሊዝምን ለመተገበርና በመንግስታት በኩል ያለው ግንኙነት የተስተካከለ እንዲሆ ለማድረግ ያግዛል ተብሏል።
በዘመን በየነ