የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

By Amele Demsew

February 27, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ድሉን በሚመጥን መልኩ መገንባቱን የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች እንዲሁም አባላት በጉብኝቱ ወቅት መናገራቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡