Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፣ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፣ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም ÷በመዲናዋ በዓለም ባንክ የሚደገፉ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ስለሚጠናቀቁበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ቴክኒካል ድጋፎችን በዘላቂነት ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፣ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ÷በኢትዮጵያ ብሎም በመዲናዋ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን ባንኩ እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸው ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው ቃል ገብተዋል፡፡

ዓለም ባንክ በመዲናዋ እየተሰሩ ላሉ የልማት ስራዎች እያደረገ ላለው ድጋፍ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በቆይታቸው የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸውን ከከንቲባዋ ማህበራዊ ተስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version