ቴክ

በኢትዮጵያ የበለጸገው የሕፃናት ቆዳ በሽታ ልየታ ሲስተም ደርምኔት

By Meseret Awoke

February 26, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ደርምኔት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የበለፀገ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት ነዉ፡፡

ሥርዓቱ የሕፃናት ቆዳ በሽታ ልየታን የሚሰራ እንደሆነ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ደርምኔት በሕክምናዉ አጠራር አቶፒክ ደርማታይተስ፣ ፖፑላር አርትካሪያ እና ስኬቢስ የተሰኙ የሕፃናት ቆዳ በሽታዎችን በመለየት ምርመራ እና ሕክምና መስጠት የሚያስችል ስርዓት እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

ደርምኔት በሕፃናት ቆዳ ስፔሻሊስት ሐኪሞች እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራማሪዎች ጥምረት የበለፀገ ስርዓት እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ታካሚዎች የቦታ፣ የጊዜ እና የሁኔታ መለዋወጥ ሳይገድባቸው በበይነ መረብ ትስስር አገልግሎቱን ያገኛሉም ነው የተባለው፡፡

አበልጽጎ ወደስራ ለማስገባት የሁለት ዓመት ጊዜን የፈጀው ይህ ስርዓት፥ ኢትዮጵያ ያሏትን ጥቂት የቆዳ ስፔሻሊስት ሐኪሞች እውቀትና ክህሎት ለማሽን በማስተማር ሕክምናውን ለማዘመን ማገዙም ተጠቁሟል፡፡

#Health #Technology #DermNet #Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!