አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገበያ ተደራሽነት ጥያቄዎችን ከሀገራት ዕድገት ጋር ማመጣጠን እንደሚያስፈልግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ አስገነዘቡ፡፡
በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በዱባይ ከሚካሄደው 13ኛው የዓለም አቀፉ ንግድ ድርጅት ስብሰባ አስቀድሞ በሚደረገው “የቻይና የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት” ላይ ተሳትፏል፡፡
አቶ ገብረ መስቀል በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያና በዓረብ ሀገራት መካከል ባሉ የንግድ ግንኙነቶች ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ዓለም አቀፉን የንግድ ድርጅት መቀላቀል እና በትብብር መሥራት ለዘርፉ ዕድገት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው÷ በተለይም የገበያ ተደራሽነት ጥያቄዎችን ከሀገራት ዕድገት ጋር ማመጣጠን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያም ድርጅቱን ለመቀላቀል የምታደርገው ሂደት የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል፡፡