አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ውድድር በመጪው እሑድ በቱኒዚያ ሃማማት መካሄድ ይጀምራል፡፡
ውድድሩ ለአራት ዓመታት ተቋርጦ የቆየ ሲሆን÷ ለስድተኛ ጊዜ በቱኒዚያ ሃማማት ከተማ ከፈረንጆቹ የካቲት 25 ቀን ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በ14 ሴት እና በ14 ወንድ በአጠቃላይ በ28 አትሌቶች እንደምትወከል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በ6ኛው የአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክም ከሰዓታት በፊት ቲኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒስ ደርሷል፡፡