የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችና አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

By Meseret Awoke

February 22, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና የሰራዊት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም ፥ ኢትዮጵያ ለአንድነቷና ለሉዓላዊነቷ ታላቅ መስዋዕትነትና ገድል የተሰራላት ትልቅ የጀግንነት ታሪክም ያላት ሀገር መሆኗ የታየበት ነው ብለዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ የአልበገር ባይነትን፣ የአንድነት፣ የነጻነት ፋና ወጊ ምልክት ነው ያሉ ሲሆን ፥ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደመሆናችን ይህን ለትውልድ ለማሻገር መከላከያ ሠራዊታችን ጠንክሮ ይሰራል ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

የጎበኘነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንደ መከላከያ ሠራዊት በአባቶቻችን ጀግንነት እንድንኮራ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ልዩ የሞራልና የሀገር አደራ ስንቅ የሚሰጥ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡