የሀገር ውስጥ ዜና

የላይቤሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

February 21, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የላይቤሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም የዓድዋ ድል የአፍሪካውያን ሁሉ ድል እና ኩራት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያውን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸውሥራውንም ማድነቃቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የአዲስ አበበ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉብኝቱ ወቅት ገለጻ አድርገዋል፡፡

የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሴት ፕሬዚዳንት የሆኑትን የላይቤሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የዓድዋ ድል መታሰቢያን በማስጎብኘታችን ደስ ብሎናል ሲሉ ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡